By ዮሐንስ አንበርብር

– ትውልደ ኢትዮጵያውያኑ ከሐምሌ ወር ጀምሮ የሚያገኙትን ትርፍ መንግሥት ይወርሰዋል

– የአክሲዮን ድርሻቸው ግን በገዙበት ዋጋ እንዲመለስ ተወስኗል

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባለፈው ሳምንት ለሁሉም የግል ባንኮችና ኢንሹራንስ ኩባንያዎች በላከው መመርያ፣ በባንኮችና በኢንሹራንሶች ውስጥ ባለድርሻ የሆኑ ዜግነት የሌላቸው ትውልደ ኢትዮጵያውያንን ከባለድርሻነት እንዲያስወጡ ወይም የአክሲዮን ድርሻቸውን እንዲሰርዙ አዘዘ፡፡

በብሔራዊ ባንክ ዋና ገዥ አቶ ተክለወልድ አጥናፉ ፊርማ የወጣው መመርያ ‹‹Manner of Relinquishing Shareholdings of Foreign Nationals of Ethiopian Origin Guideline No FIS/01/2016›› የሚል ሲሆን፣ የተገለጹት የገንዘብ ተቋማት ዜግነት የሌላቸው ትውልደ ኢትዮጵያውያን የያዙትን የአክሲዮን ድርሻ በሁለት ወራት ውስጥ ወደራሳቸው በማዞር ከባለድርሻነት እንዲያስወጧቸው የሚያዝ ነው፡፡

በባንክ ሥራ አዋጅ ቁጥር 592/2000 እና በኢንሹራንስ ሥራ አዋጅ ቁጥር 746/2004 መሠረት ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ዜግነት የሌለው በባንክና በኢንሹራንስ የሥራ ዘርፎች የባለቤትነት ድርሻ እንዳይኖረው የሚገድብ ቢሆንም፣ ዜግነት የሌላቸው ትውልደ ኢትዮጵያውያን ከሕጉ በተቃራኒ በተለያዩ ባንኮችና በኢንሹራንስ ኩባንያዎች ውስጥ የአክሲዮን ድርሻ ይዘው መገኘታቸው መረጋገጡን መመርያው ይገልጻል፡፡

‹‹ይህ ሕግን የተላለፈ ድርጊት የወንጀል ተጠያቂነትን የሚያስከትል ቢሆንም፣ ዜግነት ሳይኖራቸው በኢትዮጵያ የገንዘብ ተቋማት ውስጥ ድርሻ ያላቸው ትውልደ ኢትዮጵያውያን ላይ የወንጀል ክስ እንዳይመሠረት መንግሥት ወስኗል፤›› በማለት ለገንዘብ ተቋማቱ የተላከው ማስፈጸሚያ መመርያ ይገልጻል፡፡

በተጨማሪነት መንግሥት ባስተላለፈው ውሳኔም ዜግነት የሌላቸው ትውልደ ኢትዮጵያውያን በባንኮችና በኢንሹራንስ ኩባንያዎች ውስጥ ያላቸው ኢንቨስትመንት እንዲቀለበስ፣ እንዲሁም በትውልደ ኢትዮጵያውያኑ የተያዙትን አክሲዮኖች ያመነጩ ባንኮችና ኢንሹራንስ ኩባንያዎች አክሲዮኖቹን ባቀረቡበት ወቅት በነበረው ዋጋ መሠረት ለትውልደ ኢትዮጵያውያኑ ገንዘባቸውን እንዲመልሱና እ.ኤ.አ. እስከ ጁን 2016 መጨረሻ ድረስ ሊያገኙ የሚችሉትን የትርፍ ድርሻ እንዲከፍሉ አዟል፡፡

በማስፈጸሚያ መመርያው መሠረት ኢትዮጵያዊ ዜግነት የሌላቸው ትውልደ ኢትዮጵያውያን ማለት ኢትዮጵያዊ ዜግነትን በመቀየር ኤርትራዊ ዜግነትን ካገኙት በስተቀር፣ ማንኛውም የውጭ ዜግነት ከማግኘቱ በፊት ኢትዮጵያዊ ዜግነት የነበረው ወይም ከወላጁ ወይም ከአያቶቹ ወይም ከቅድመ አያቶቹ ቢያንስ አንዱ ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያለው (የነበረው) ስለመሆኑ ትርጓሜ ተሰጥቶታል፡፡

ዜግነት የሌላቸው ትውልደ ኢትዮጵያውያን የያዟቸው አክሲዮኖች እ.ኤ.አ. እስከ ጁን 30 ቀን 2016 የሚያስገኘው የትርፍ ድርሻ ሊከፈል የሚችለው በኢትዮጵያ ብር ብቻ መሆኑንም መመርያው ያስቀምጣል፡፡ ከጁን 30 ቀን 2016 በኋላ የአክሲዮን ድርሻቸው የሚያስገኘው የትርፍ ድርሻ የኢትዮጵያ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር በብሔራዊ ባንክ ውስጥ ባለው የመንግሥት ግምጃ ቤት ሒሳብ እንዲያስገቡ የገንዘብ ተቋማቱ ታዘዋል፡፡

መመርያው ተግባራዊ እንዲሆን ከታዘዘበት እ.ኤ.አ. ኦክቶበር 28 ቀን 2016 ጀምሮ ቢያንስ ለአራት ጊዜ በቂ ተደራሽነት ባላቸው ጋዜጦች፣ ዜግነት የሌላቸው ትውልደ ኢትዮጵያውያን ያላቸውን የአክሲዮን ድርሻ እንዲወስዱ የገንዘብ ተቋማቱ ጥሪ ማድረግ እንዳለባቸው አሳስቧል፡፡

የገንዘብ ተቋማቱ የጥሪ ማስታወቂያውን ለመጀመሪያ ጊዜ ካወጡበት ቀን አንስቶ በ60 የሥራ ቀናት ውስጥ የአክሲዮን ድርሻ ያላቸው ዜግነት የሌላቸው ትውልደ ኢትዮጵያውያን የአክሲዮን ባለድርሻነታቸውን የሚገልጽ ሠርተፍኬት በማቅረብ፣ የአክሲዮን ድርሻቸውን ለገንዘብ ተቋማቱ በማስተላለፍ ድርሻቸውን አክሲዮኑን በገዙበት ዋጋ እንዲወስዱ አሳስቧል፡፡

በተቀመጠው 60 የሥራ ቀናት ውስጥ ወደ ገንዘብ ተቋማቱ በመቅረብ የአክሲዮን ድርሻቸውን ያላዘዋወሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያን የአክሲዮን ድርሻን የገንዘብ ተቋማቱ እንዲሰርዙ፣ ይህንንም ስለማድረጋቸው በዝርዝር የሚያስረዳ ማስታወቂያ ተደራሽነት ባለው ጋዜጣ ቢያንስ አንድ ጊዜ ማውጣት እንዳለባቸው መመርያው ይገልጻል፡፡

መቅረብ ያልቻሉ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ግን የአክሲዮን ድርሻቸውን መጠን በገዙበት ዋጋ፣ እንዲሁም እ.ኤ.አ. እስከ ጁን 30 ቀን 2016 ድረስ ያፈራላቸውን የትርፍ ድርሻ በማንኛውም ጊዜ በመቅረብ የገንዘብ ተቋማቱ ሕግን መሠት አድርገው የአክሲዮን ሽያጫቸውን እስካከናወኑ ድረስ መልሰው ማግኘት እንደሚችሉ መመርያው ያስረዳል፡፡

ዜግነት የሌለው ትውልደ ኢትዮጵያዊ ሆን ብሎ ዜግነት እንዳለው የሚያሳዩ መረጃዎችን በማቅረብ የአክሲዮን ድርሻው እንዲቀጥል ማድረጉ ከታወቀ፣ የአክሲዮን ድርሻውንም ሆነ የትርፍ ድርሻውን ማግኘት እንደማይችል ብሔራዊ ባንክ ለገንዘብ ተቋማቱ የላከው ማስፈጸሚያ መመርያ ይገልጻል፡፡

የአክሲዮን ድርሻ ያላቸው ትውልደ ኢትዮጵያውያን ኢትዮጵያዊ ዜግነት እንዳላቸው ለማስመሰል አቅደው የሚያደርጉትን የማጭበርበር ሙከራ ያወቁ ባንኮችና ኢንሹራንስ ኩባንያዎች ከተገቢ ማስረጃዎቻቸው ጋር በአምስት የሥራ ቀናት ውስጥ ለብሔራዊ ባንክ ማሳወቅ እንዳለባቸው አስታውቋል፡፡

ትውልደ ኢትዮጵያውያኑ ሆን ብለውና አቅደው ሊያቀርቡ ከሚችሏቸው ማስረጃዎች መካከል የቀበሌ መታወቂያና በማንኛቸውም የመንግሥት ተቋማት ሊዘጋጁ የሚችሉ ማስረጃዎች እንደሚሆኑ በምሳሌነት በመመርያው ላይ ተቀምጧል፡፡ በተቀመጠው 60 የሥራ ቀናት የጊዜ ገደብ ውስጥ ትውልደ ኢትዮጵያውያኑ ያስተላለፉዋቸውን የአክሲዮን ድርሻዎች፣ ባንኮቹና የኢንሹራንስ ኩባንያዎቹ የውስጥ ፖሊሲዎቻቸውንና አሠራሮቻቸውን ተከትለው የተላለፉላቸውን አክሲዮኖች በግልጽ ጨረታ ለገበያ ማቅረብ እንደሚችሉ ፈቅዷል፡፡

እነዚህ የተላለፉ አክሲዮኖች በግልጽ ጨረታ ስለመሸጣቸው ብሔራዊ ባንክ ክትትል የሚያደርግ መሆኑንና በድርድር መሸጥ እንደማይቻል አስታውቋል፡፡

ብሔራዊ ባንክ ዜግነት በሌላቸው ትውልደ ኢትዮጵያውያን የአክሲዮን ድርሻ ላይ ያስተላለፈው ይህ የመጨረሻ ውሳኔ በገንዘብ ተቋማቱ ላይ የሚያደርሰው ጉዳት እንደማይኖር ባለሙያዎች ይገልጻሉ፡፡ ለዚህ የሚሰጡት ምክንያት የገንዘብ ተቋማቱ የትውልደ ኢትዮጵያውያኑን የአክሲዮን ድርሻ መልሰው ለገበያ የሚያቀርቡ መሆኑንና ይህንንም ሲያደርጉ አሁን ባለው የገበያ ዋጋ በመሆኑ ጉዳት እንደማያገኛቸው ያስረዳሉ፡፡

ብሔራዊ ባንክ ያስተላለፈው ውሳኔ በኢትዮጵያ በገንዘብ ተቋማት ውስጥ ማንኛውም የውጭ አገር ዜጋ የባለቤትነት ድርሻ ሊኖረው እንደማይችል በሕግ ገደብ መጣሉን ቢሆንም፣ የግል ባንኮች የገንዘብ ንግድ ሥራ ከተፈቀደ ከ20 ዓመታት በኋላ የትውልደ ኢትዮጵያውያን ባለድርሻ መሆን አሁን እንዴት ለመንግሥት ሥጋት ሊሆን እንደቻለ እንቆቅልሽ እንደሆነባቸው አስረድተዋል፡፡

የውጭ ዜጎች በኢትዮጵያ የገንዘብ ተቋማት ውስጥ በባለድርሻነትም ሆነ በባለቤትነት እንዳይሳተፉ የተከለከለበት ዓብይ ምክንያት፣ አገር በቀል የገንዘብ ተቋማት እንዲጠናከሩ ከለላ ለመስጠትና በዘርፉ የመንግሥት የመቆጣጠር አቅም እስኪገነባ ድረስ የተወሳሰበ ልምድ ያላቸው የውጭ ባንኮች ለአገሪቱ ማክሮ ኢኮኖሚ ሥጋት እንዳይፈጥሩ መሆኑን ባለሙያዎቹ ያብራራሉ፡፡

ይህ ቢሆንም መንግሥት የዓለም ንገድ ድርጅትን ለመቀላቀል እያደረገ ባለው ድርድር እስከ ቅርብ ጊዜ ለውጭ ዜጎች አይከፈቱም ካላቸው የቴሌኮምና የገንዘብ ተቋማት ሥራ መካከል፣ የገንዘብ ተቋማት የሥራ ዘርፍን በድርድር ለመክፈት መንግሥት ፍላጎቱን ከመግለጹ በተጨማሪም በሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ማብቂያ ላይ የዓለም የንግድ ድርጅት የኢትዮጵያ አባልነት ድርድርን ለማጠናቀቅ ግብ ማስቀጡን ያስረዳሉ፡፡

መንግሥት ዘርፉን ለመክፈት ፍላጎት አሳይቶ ሳለ ትውልደ ኢትዮጵያውያንን ከዓመታት ቆይታ በኋላ በገንዘብ ተቋማት ውስጥ ያላቸው የአክሲዮን ድርሻ እንዲተላለፍ ለመወሰን ያስፈለገበት ምክንያት ግር እንዳሰኛቸው ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

የቆየ ስህተትን አሁን በማረም ሕጋዊ አሠራርን ማስፈን ምክንያት ሊሆን አይችልም ማለታቸው እንዳልሆነ የሚገልጹት ባለሙያዎቹ፣ ቢያንስ ትውልደ ኢትዮጵያውያኑ የአክሲዮን ድርሻቸውን ለኢትዮጵያዊ ቤተሰቦቻቸው በሕጋዊ ሥርዓት እንዲያስተላልፉ በአማራጭ ውሳኔነት አለመካተቱ እንዳስገረማቸው ተናግረዋል፡፡

Subscribe or Rent movies to watch. Monthly Subscription - 20 አዳዲስ + 6 ተጨማሪ ፊልሞች በየወሩ እና ከዚህ በፊት የተለቀቁ ከ400 በላይ ፊልሞችን ሆነ ሌሎች ቪድዮዎችን በፈለጋችሁት ሰዓት፣ ያሻችሁን ያህል ደጋግማች በቲቪ፣ ተንቀሳቃሽ ስልክ ወይም ኮምፒውተር ተመልከቱ። የአንድ ወር ከፍላቹህ በፈለጋችሁት ሰዓት ማቋረጥ ትችላላቹህ። Watch 20 new + additional 6 movies per month and more than 400 Ethiopian movies. You can watch when you want, as much as you want on TV, mobile phone, tablet or computer. Subscribe for one month and cancel anytime. Monthly subscription prices are $4.99, $19.99 or $29.99. Rent price starts at $2.99. 29.99/month - 20 new after sign up + 6 new movies per month and 400+ released films የሶደሬ ደንበኛ የምትሆኑት ለመጀመርያ ጊዜ ከሆነ እስከ 20 አዳዲስ ፊልሞች+ 6 ተጨማሪ ፊልሞች በየወሩ እና ከዚህ በፊት የተለቀቁ ከ400 በላይ ፊልሞች KIDS videos የልጆች ቪድዮዎች   Movie premier videos የፊልም ምርቃት ቪድዮውች 19.99/month - 4 new movie after sign up + 4 new movies per month and 400+ released films የሶደሬ ደንበኛ የምትሆኑት ለመጀመርያ ጊዜ ከሆነ እስከ 4 አዳዲስ ፊልሞች + 4 ተጨማሪ ፊልሞች በየወሩ እና ከዚህ በፊት የተለቀቁ ከ400 በላይ ፊልሞች  4.99/month - 2 new movies after sign up + 2 new movies per month and 400+ released films የሶደሬ ደንበኛ የምትሆኑት ለመጀመርያ ጊዜ ከሆነ 2 አዳዲስ ፊልሞች + 2 ተጨማሪ ፊልሞች በየወሩ እና ከዚህ በፊት የተለቀቁ ከ400 በላይ ፊልሞች All videos on SodereTube with no Advertisement ሶደሬቲዩብ ላይ ያሉ ሁሉንም ቪድዮችን ያለ ማስተወቂያ ማየት ይቻላል There are three options to pay: PayPal, credit card or Bank Transfer. ክፍያውን በሶስት መንገድ መክፈል ይቻላል - በፔይፓል፣ ክሬዲት/ዴት ካርድ ወይም በባንክ ቁጥር ማስተላለፍ። To pay through credit card or PayPal, click SUBSCRIBE NOW button, add cart and "proceed to check out", Enter your name, address and other information. ለመክፈል ሰማያዊውን ተጫኑ፣ አድ ቱ ካርት፣ ፕሮሲድ ቱ ቼክ አውት ከዚያ ስማችሁን፣ አድራሻ፣ የፔይፓል ወይም የካርድ መረጃውን አስገቡ። subscribenow Rent and Watch. Price starts at $2.99. ተከራይቶ ለማየት If you pay with bank deposit, you have to pay $100 which allow you to be a subscriber for 3 months and $10 processing fee. To pay using bank deposit, click here. ክፍያ ላይ ችግር ካጋጠማቹህ በዚህ ስልክ ቁጥር ደውሉ። Questions? call 1 310 570 9291 viber or direct. For detailed description and list of movie on SodereOnDemand read this. ስለ ሶደሬ ኦን ዲማንድ የበለጠ ለማወቅ ይህን መረጃ አንብቡ።

Receive Ethiopian News, Movies and Videos by email. Sign up for Email alerts

ትኩስ እና ሰበር ዜና፣ በብዛት የታዩ ቪድዮዎች፣ ፊልሞች፣ ድራማዎች፣ ሙዚቃዎች፣ ጠቃሚ ምክሮችን እና አስገራሚ ታሪኮችን በቀን አንዴ በኢሜል አድራሻችሁ እንልካለን።