አዲስ አበባ ፣ ህዳር 15 ፣ 2009 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ7 ሚሊየን ብር በላይ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሁለት ቅርንጫፎች በራሳቸው ሂሳብ አዘዋውረው የተከፋፈሉ ስምንት ግለሰቦና 5 የግል ድርጅቶች በጽኑ እስራት እና በገንዘብ ተቀጡ።

ተከሳሾች 1ኛ ታምርአየሁ ተክሌ፣ 2ኛ ኤፍሬም ወልደተንሳይ፣ 3ኛ ንብረት ማሞን ጨምሮ ስምንት ተከሳሾችና አምስት በግንባታ ዘርፍ የተሰማሩ የግል ድርጅቶች ናቸው።

የቀድሞው የስነ ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሸን አቃቢ ህግ በክሱ ላይ እንዳመለክተው 1ኛና 2ኛ ተከሳሾች ከ2005 እስከ 2007 ዓ.ም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋናው መስሪያ ቤት እና የቅርንጫፍ አግልግሎት ስራ አስኪያጅና ሲኒዬር ኦፊሰር በመሆን ሲሰሩ የቆዩ ናቸው።

3ኛ፣ 4ኛ፣ 5ኛ እና 8ኛ ተከሳሾች በግል ስራ የሚተዳደሩ ሲሆን፥ 6ኛ ተከሳሸ ደግሞ በደቡብ ክልል የውሃ ሃብት ቢሮ ባለሙያ ነው።

ተከሳሾቹ ዝምድናቸውን በመጠቀም በዋናው መስሪያ ቤት ውስጥ ከሂሳብ እየተቀነሰ ወደተለያዩ ቅርጫፎች የሚገባውን የሂሳብ ማስታረቂያ እንዲሰሩ የተሰጣቸውን ሃላፊነት ተጠቅመው የባንኩን ሂሳብ ያለአግባብ ወጪ በማድረግ ታቦር ቅርጫፍ በሚገኘው 3ኛ እና 6ኛ ተከሳሾች የባንክ አካውንት ገንዘብ ማስገባታቸው ተጠቅሷል።

በዚህም 3ኛ እና 6ኛ ተከሳሾች ባቋቋሙት የ9ኛ ተከሳሽ ዲባሲ ጠቅላላ ኮንስትራክሽን ማህበር አካውንት ውስጥ፥ ስድስት ሚሊየን ስድስት መቶ ሰባ አራት ሺህ አራት መቶ አንድ ብር ከሃያ ስድስት ሳንቲም እንዲገባ ማድረጋቸው ነው በክሱ የተጠቀሰው።

እንዲሁም ከአዲስ አበባ ጠመንጃ ያዥ ቅርንጫፍ በሚገኝ 13ኛ ተከሳሽ ወንድምአገኝ ዲዛ ኮንስትራክሸን ስም የተከፈተ ሂሳብ ሶስት መቶ ዘጠና ሺህ አራት መቶ ሃምሳ ስድስት ብር ከሰላሳ ዘጠኝ ሳንቲም በአጠቃላይ ሰባት ሚሊየን ስልሳ አራት ሺህ ስምንት መቶ ሃምሳ ሰባት ብር ከስልሳ አምስት ሳንቲም በህገወጥ መንገድ እንዲዘዋወር ማድረጋቸው የኮሚሽኑ ከሳሽ አቃቢ ህግ ዝርዝር ያስረዳል።

ያዘዋወሩትን ገንዘብም በ3ኛ ተከሳሽ አማካኝነት በማውጣትና በመከፋፈል በመንግስትና በህዝብ ላይ ተመሳሳይ የገንዘብ ጉዳት እንዲደርስ አድርገዋል ሲልም ነው አቃቢ ህግ በክሱ የጠቀሰው።

አቃቢ ህግ ያቀረበውን የሰውና የሰነድ ማስረጃን እና የተከሳሾች መከላከያ የተከታተለው የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 18ኛ ወንጀል ችሎት ተከሳሾቹን በተከሰሱበት ወንጀል ጥፋተኛ ብሏቸዋል።

በዚህም ለ1ኛ ተከሳሽ ሶስት ማቅለያ በመያዝ በ4 አመት ጽኑ እስራትና በ7 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ፣ 2ኛ ተከሳሽን አንድ ማቅለያ በመያዘ በ17 አመት ጽኑ እስራትና በ60 ሺህ ብር፣ 3ኛ ተከሳሽን በ11 አመት ጽኑ እስራትና በ35 ሺህ ብር፣ 4ኛ ተከሳሽን 4 ማቅለያ በመያዝ በ7አመት ጽኑ እስራትና በ20 ሺህ ብር እንዲቀጡ ወስኗል።

5ኛ ተከሳሽ ደግሞ ነፍሰ ጡር ሆና በማረሚያ ቤት በአስቸጋሪ ሁኔታ የወለደቻት ህጻን መሞቷን በማቅለያነት በመያዝ በሁለት አመት ገደብ፣ 6ኛ እና 8ኛ ተከሳሾችን እያንዳንዳቸውን በ16 አመት ጽኑ እስራትና በ50 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ ወስኖባቸዋል።

በሶስተኛ ተከሳሽ በስራ አስኪያጅነት የሚመራው 9ኛ ተከሳሽ ጂ ቢ ሲ ጠቅላላ ኮንስትራክሽን ማህበር በ350 ሺህ ብር እንዲቀጡ ወስኗል።

10ኛ ተከሳሸ ንብረት ማሞ የኮንስትራክሽን ማሸነሪ አከራይ የግል ማህበር፣ በ1ኛ ተከሳሽ ስራ አስኪያጅነት የሚመራው 11ኛ ተከሳሽ አዳነና ቤተሰቦቹ የኮንስትራክሽን ማሸነሪ አከራይ የግል ማህበር፣ በ4ኛ ተከሳሽ ስራ አስኪያጅነት የሚመራው 12ኛ ተከሳሽ ሄኖክ ወልደተንሳይ የኮንስትራክሽን ማሸነሪ አከራይ የግል ማህበር፣ በ8ኛ ተከሳሽ የሚመራው 13ኛ ተከሳሽ ወንድምአገኝ ዲዛ ህንጻ ኮንስትራክሽን ድርጅት እያንዳንዳቸው በ125 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡ ውሳኔ አስተላልፏል።

በችሎቱ ያልተገኙት 2ኛ፣ 6ኛ እና 8ኛ ተከሳሾችን የፌደራል ፖሊስ ካሉበት ይዞ ለማረሚያ ቤቱ እንዲያስረክብም ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ አስተላልፏል።

በታሪክ አዱኛ

Subscribe or Rent movies to watch. Monthly Subscription - 20 አዳዲስ + 6 ተጨማሪ ፊልሞች በየወሩ እና ከዚህ በፊት የተለቀቁ ከ400 በላይ ፊልሞችን ሆነ ሌሎች ቪድዮዎችን በፈለጋችሁት ሰዓት፣ ያሻችሁን ያህል ደጋግማች በቲቪ፣ ተንቀሳቃሽ ስልክ ወይም ኮምፒውተር ተመልከቱ። የአንድ ወር ከፍላቹህ በፈለጋችሁት ሰዓት ማቋረጥ ትችላላቹህ። Watch 20 new + additional 6 movies per month and more than 400 Ethiopian movies. You can watch when you want, as much as you want on TV, mobile phone, tablet or computer. Subscribe for one month and cancel anytime. Monthly subscription prices are $4.99, $19.99 or $29.99. Rent price starts at $2.99. 29.99/month - 20 new after sign up + 6 new movies per month and 400+ released films የሶደሬ ደንበኛ የምትሆኑት ለመጀመርያ ጊዜ ከሆነ እስከ 20 አዳዲስ ፊልሞች+ 6 ተጨማሪ ፊልሞች በየወሩ እና ከዚህ በፊት የተለቀቁ ከ400 በላይ ፊልሞች KIDS videos የልጆች ቪድዮዎች   Movie premier videos የፊልም ምርቃት ቪድዮውች 19.99/month - 4 new movie after sign up + 4 new movies per month and 400+ released films የሶደሬ ደንበኛ የምትሆኑት ለመጀመርያ ጊዜ ከሆነ እስከ 4 አዳዲስ ፊልሞች + 4 ተጨማሪ ፊልሞች በየወሩ እና ከዚህ በፊት የተለቀቁ ከ400 በላይ ፊልሞች  4.99/month - 2 new movies after sign up + 2 new movies per month and 400+ released films የሶደሬ ደንበኛ የምትሆኑት ለመጀመርያ ጊዜ ከሆነ 2 አዳዲስ ፊልሞች + 2 ተጨማሪ ፊልሞች በየወሩ እና ከዚህ በፊት የተለቀቁ ከ400 በላይ ፊልሞች All videos on SodereTube with no Advertisement ሶደሬቲዩብ ላይ ያሉ ሁሉንም ቪድዮችን ያለ ማስተወቂያ ማየት ይቻላል There are three options to pay: PayPal, credit card or Bank Transfer. ክፍያውን በሶስት መንገድ መክፈል ይቻላል - በፔይፓል፣ ክሬዲት/ዴት ካርድ ወይም በባንክ ቁጥር ማስተላለፍ። To pay through credit card or PayPal, click SUBSCRIBE NOW button, add cart and "proceed to check out", Enter your name, address and other information. ለመክፈል ሰማያዊውን ተጫኑ፣ አድ ቱ ካርት፣ ፕሮሲድ ቱ ቼክ አውት ከዚያ ስማችሁን፣ አድራሻ፣ የፔይፓል ወይም የካርድ መረጃውን አስገቡ። subscribenow Rent and Watch. Price starts at $2.99. ተከራይቶ ለማየት If you pay with bank deposit, you have to pay $100 which allow you to be a subscriber for 3 months and $10 processing fee. To pay using bank deposit, click here. ክፍያ ላይ ችግር ካጋጠማቹህ በዚህ ስልክ ቁጥር ደውሉ። Questions? call 1 310 570 9291 viber or direct. For detailed description and list of movie on SodereOnDemand read this. ስለ ሶደሬ ኦን ዲማንድ የበለጠ ለማወቅ ይህን መረጃ አንብቡ።

Receive Ethiopian News, Movies and Videos by email. Sign up for Email alerts

ትኩስ እና ሰበር ዜና፣ በብዛት የታዩ ቪድዮዎች፣ ፊልሞች፣ ድራማዎች፣ ሙዚቃዎች፣ ጠቃሚ ምክሮችን እና አስገራሚ ታሪኮችን በቀን አንዴ በኢሜል አድራሻችሁ እንልካለን።