Written by አለማየሁ አንበሴ (Addis Admass News)
በአዲስ አበባ ሳሪስ አካባቢ የኢንተርኔት ካፌ ከፍቶ መስራት ከጀመረ 7 ዓመታት ያስቆጠረው ስሙ እንዳይጠቀስ የጠየቀ ወጣት፤ በየዓመቱ በዚህ ወቅት የአሜሪካን ዲቪ ሎተሪ በማስሞላት ዳጎስ ያለ ገቢ ያገኝ እንደነበር ይናገራል፡፡ ዘንድሮ ግን በከተማዋ የኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጡን ተከትሎ፣ የተለመደውን አገልግሎት ለደንበኞቼ መስጠት እንዳልቻለ ይገልፃል፡፡ በአማራጭነት የዋይ ፋይ አገልግሎት መስጫ ቢኖረውም በአግባቡ የሚሰራ ባለመሆኑ፣ እንኳን ዲቪ ለማስሞላት ይቅርና የኢንተርኔት አገልግሎት በቅጡ ለመስጠት አዳግቶኛል ብሏል፡፡
የኢንተርኔት አገልግሎት በመስጠት ብቻ በቀን በአማካይ ከ300-500 ብር ገቢ ያገኝ እንደነበር የሚናገረው የኢንተርኔት ካፌ ባለቤት፤ የኢንተርኔት መቋረጥ የሥራ ዘርፉን እንዳስቀየረው ይናገራል። “የኮምፒውተር ፅሁፍ፣ መጠረዝና፣ የፎቶ ኮፒ ስራዎችን ብቻ ለመስራት ተገድጄአለሁ” ብሏል። በየአመቱ ጥሩ ገቢ ያስገኝለት የነበረው ዲቪ የማስሞላት ስራም በኢንተርኔት መቋረጥ ሳቢያ መስተጓጎሉን ገልጿል፡፡
የዲቪ አመልካቾች በኢንተርኔት መቋረጥ የገጠማቸውን ችግር በተመለከተ ለአሜሪካ ኤምባሲ ላቀረብነው ጥያቄ፤ ችግሩ ከዲቪ ማመልከቻ ድረ ገፁ ሳይሆን ከኢንተርኔት መንቀራፈፍና መቆራረጥ ጋር የተያያዘ ነው ብሏል፡፡
“አመልካቾች የ2018 የአሜሪካ ዲቪ ሎተሪ ማመልከቻን በኢንተርኔት ሞልተው ለመላክ ችግር ሊገጥማቸው እንደሚችል እንገነዘባለን፡፡ ይሄ አስቸጋሪ ሁኔታ በመከሰቱም በእጅጉ እናዝናለን፡፡ ችግሩ ያለው ከእኛ ድረ-ገፅ አይደለም፤ ከኢንተርኔት መቆራረጥና መንቀራፈፍ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ አመልካቾች የተሻለ የኢንተርኔት ግንኙነት ለማግኘት በቀን ውስጥ በተለያዩ ጊዜያት ሙከራቸውን በትዕግስት እንዲገፉበት እንመክራለን፡፡ ከኢንተርኔት ካፌዎች ወይም ከሌሎች የኢንተርኔት ማዕከሎች አገልግሎቱን ለማግኘት ቢሞክሩም አይከፋም፡፡ ለዲቪ አመልካቾች መልካም ዕድል እየተመኘን፣ ማንኛውም አመልካች ከጥቅምት 28 ቀን 2009 ዓ.ም በፊት ማመልከቻውን ሞልቶ መላክ እንዳለበት ለማስታወስ እንወዳለን” ብሏል ኤምባሲው፡፡
የኢንተርኔት መቋረጥን በተመለከተ ለኢትዮ ቴሌኮም ላቀረብንለት ጥያቄ በሰጠው ምላሽ፣ “እስካሁን ከደንበኞቼ የቀረበልኝ ቅሬታ የለም” ብሏል፡፡ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ከሰሞኑ፤ በኢትዮጵያ የኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጡን ሲዘግቡ መሰንበታቸው ይታወሳል፡፡

Subscribe or Rent movies to watch. Monthly Subscription - 20 አዳዲስ + 6 ተጨማሪ ፊልሞች በየወሩ እና ከዚህ በፊት የተለቀቁ ከ400 በላይ ፊልሞችን ሆነ ሌሎች ቪድዮዎችን በፈለጋችሁት ሰዓት፣ ያሻችሁን ያህል ደጋግማች በቲቪ፣ ተንቀሳቃሽ ስልክ ወይም ኮምፒውተር ተመልከቱ። የአንድ ወር ከፍላቹህ በፈለጋችሁት ሰዓት ማቋረጥ ትችላላቹህ። Watch 20 new + additional 6 movies per month and more than 400 Ethiopian movies. You can watch when you want, as much as you want on TV, mobile phone, tablet or computer. Subscribe for one month and cancel anytime. Monthly subscription prices are $4.99, $19.99 or $29.99. Rent price starts at $2.99. 29.99/month - 20 new after sign up + 6 new movies per month and 400+ released films የሶደሬ ደንበኛ የምትሆኑት ለመጀመርያ ጊዜ ከሆነ እስከ 20 አዳዲስ ፊልሞች+ 6 ተጨማሪ ፊልሞች በየወሩ እና ከዚህ በፊት የተለቀቁ ከ400 በላይ ፊልሞች KIDS videos የልጆች ቪድዮዎች   Movie premier videos የፊልም ምርቃት ቪድዮውች 19.99/month - 4 new movie after sign up + 4 new movies per month and 400+ released films የሶደሬ ደንበኛ የምትሆኑት ለመጀመርያ ጊዜ ከሆነ እስከ 4 አዳዲስ ፊልሞች + 4 ተጨማሪ ፊልሞች በየወሩ እና ከዚህ በፊት የተለቀቁ ከ400 በላይ ፊልሞች  4.99/month - 2 new movies after sign up + 2 new movies per month and 400+ released films የሶደሬ ደንበኛ የምትሆኑት ለመጀመርያ ጊዜ ከሆነ 2 አዳዲስ ፊልሞች + 2 ተጨማሪ ፊልሞች በየወሩ እና ከዚህ በፊት የተለቀቁ ከ400 በላይ ፊልሞች All videos on SodereTube with no Advertisement ሶደሬቲዩብ ላይ ያሉ ሁሉንም ቪድዮችን ያለ ማስተወቂያ ማየት ይቻላል There are three options to pay: PayPal, credit card or Bank Transfer. ክፍያውን በሶስት መንገድ መክፈል ይቻላል - በፔይፓል፣ ክሬዲት/ዴት ካርድ ወይም በባንክ ቁጥር ማስተላለፍ። To pay through credit card or PayPal, click SUBSCRIBE NOW button, add cart and "proceed to check out", Enter your name, address and other information. ለመክፈል ሰማያዊውን ተጫኑ፣ አድ ቱ ካርት፣ ፕሮሲድ ቱ ቼክ አውት ከዚያ ስማችሁን፣ አድራሻ፣ የፔይፓል ወይም የካርድ መረጃውን አስገቡ። subscribenow Rent and Watch. Price starts at $2.99. ተከራይቶ ለማየት If you pay with bank deposit, you have to pay $100 which allow you to be a subscriber for 3 months and $10 processing fee. To pay using bank deposit, click here. ክፍያ ላይ ችግር ካጋጠማቹህ በዚህ ስልክ ቁጥር ደውሉ። Questions? call 1 310 570 9291 viber or direct. For detailed description and list of movie on SodereOnDemand read this. ስለ ሶደሬ ኦን ዲማንድ የበለጠ ለማወቅ ይህን መረጃ አንብቡ።

Receive Ethiopian News, Movies and Videos by email. Sign up for Email alerts

ትኩስ እና ሰበር ዜና፣ በብዛት የታዩ ቪድዮዎች፣ ፊልሞች፣ ድራማዎች፣ ሙዚቃዎች፣ ጠቃሚ ምክሮችን እና አስገራሚ ታሪኮችን በቀን አንዴ በኢሜል አድራሻችሁ እንልካለን።