በልደታ ኮንደሚኒየም “ጭፈራ ቤቶች” ነዋሪዎች ተማርረዋል

‹‹አካባቢው ወደፊት የዝሙትና የረብሻ መናኸሪያ እንዳይሆን እንሰጋለን›› – ነዋሪዎች

በልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 8፣ ልደታ ኮንዶሚኒየም ላይ የሚገኙ ነዋሪዎች፤ በየመኖሪያ ህንፃቸው ስር በተከፈቱ መጠጥ ቤቶዎችና ጭፈራ ቤቶች ሁካታ ሳቢያ ሰላም ማጣታቸውን ለአዲስ አድማስ ገለፁ። “አካባቢው ወደፊት የዝሙት፣ የዳንኪራና የሴተኛ አዳሪነት መናኸሪያ እንዳይሆን እንሰጋለን” ብለዋል ነዋሪዎቹ፡፡
እስከ ሌሊቱ ስምንትና ዘጠኝ ሰዓት ድረስ ከጭፈራ ቤቶቹ የሚወጣው ሁካታ፤ የኮንዶሚኒየሙ ነዋሪዎችን በተለይ ህፃናት ልጆቻቸውን በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚረብሽ ነዋሪዎቹ ተናግረዋል፡፡ በኮንዶሚኒየሙ የተለያዩ ብሎኮች ሥር የተከፈቱ “ጭፈራ ቤቶች” ሰላማዊ ህይወትን ከማናጋታቸው በተጨማሪ ለህፃናት ልጆች አስተዳደግ ፈተና እየሆኑ መሄዳቸውንም ነዋሪዎቹ ለአዲስ አድማስ ገልፀዋል።
የስድስት ልጆች እናት መሆናቸውን የተናገሩት አንዲት የኮንዶሚኒየሙ ነዋሪ፤ በዚህ ሁኔታ ልጆቻቸውን በጥሩ ስነ-ምግባር አንፀው ለማሳደግ እንደማይችሉ ጠቁመው፤ ወደፊት ነዋሪው በምሬት እየለቀቀ ፎቆቹ ወደ አልቤርጎነት መቀየራቸው አይቀርም ሲሉ ስጋታቸውን ገልፀዋል፡፡ ሌላው የአካባቢው ነዋሪ አዛውንት ሲናገሩ፤ “ቀን በአድካሚ ስራ ላይ ውዬ ምሽቱን ለማረፍ ወደ ቤት ስመለስ ሌላ ድካም ይጠብቀኛል፤ የሙዚቃው ጩኸት፣ ጭፈራና ዳንኪራው ሰላሜን ይነፍገኛል” ይላሉ፡፡ ሁኔታው በዚህ ከቀጠለ ሥፍራው ከመኖሪያ ቦታነት ይልቅ የቀለጠ መንደር ይሆናል ብለዋል፡፡
በመሸታና ጭፈራ ቤቶቹ ክፉኛ መረበሻቸውን የገለፁት የኮንዶሚኒየሙ ነዋሪዎች፤ ጉዳዩን ለወረዳ 8 ሥራ አስፈፃሚና ለክ/ከተማው ኃላፊዎች በተደጋጋሚ ማመልከታቸውንና ኃላፊዎቹ መጥተው ማስጠንቀቂያ ሲሰጧቸው፣ ለአንድ ሁለት ቀናት ሁኔታው ተስተካክሎ ወዲያው ወደነበረበት እንደሚመለስ በምሬት ተናግረዋል፡፡
የልደታ ክ/ከተማ አካባቢ ጥበቃ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ገ/ማሪያም ወ/አረጋይ ችግሩ መኖሩን እንደሚያውቁ ገልፀው፣ በአካባቢው ከፍተኛ የድምፅ መጠን ከሚጠቀሙ ሰባት ድርጅቶች መካከል በሶስቱ ላይ ‹‹ዴሲቤል›› በተሰኘው የድምፅ መለኪያ መሳሪያ ድምፁ ተለክቶ ከተገቢው በላይ መሆኑ መረጋገጡን ተናግረዋል፡፡ ከዚህ ቀደም አንዱ ድርጅት እንዲዘጋ ከወሰንን በኋላ “ከጥፋቴ እማራለሁ፤ አስተካክላለሁ” ብሎ ይቅርታ ስለጠየቀ ምህረት ተደርጎለት ነበር ብለዋል፡፡ በቀሩት ድርጅቶች ላይ ልኬቱን አካሂደን እርምጃ እንወስዳለን ያሉት ኃላፊው፤ የድምፅ ብክለት ብቻ ሳይሆን ማህበራዊ እሴትን የሚፈታተኑ አስነዋሪ ድርጊቶች እንደሚካሄዱ መስማታቸውንም ገልፀዋል፡፡ “ከወረዳው ስራ አስፈፃሚና ከንግድ ፅ/ቤት ጋር በመመካከር ዘላቂ እርምጃ ለመውሰድና በማህበረሰቡ ላይ የአስተሳሰብ ለውጥ ለማምጣት በዝግጅት ላይ ነን” ሲሉ ሃላፊው ተናግረዋል፡፡
ብዙ ነዋሪዎች ባሉበትና ለመኖሪያነት በተከለሉ ቦታዎች ላይ ለጭፈራ ቤቶች የንግድ ፈቃድ መስጠት አግባብ ነው ወይ? ተብለው የተጠየቁት የወረዳው የንግድ ጽ/ቤት፤ መጀመሪያ ፈቃድ ሲጠይቁ ለካፌ፣ ለምግብ ቤት፤ ለግሮሰሪና ለመሳሰሉት እያሉ ስለሚወስዱ ነው እንጂ ለጭፈራ ቤት ፈቃድ አይሰጥም ብለዋል፡፡ ቤቶቹ ቀን ቀን በምግብ ቤትነትና በካፌነት አገልግሎት ሲሰጡ ቆይተው፣ ማታ ወደ ጭፈራ ቤትነት የሚቀይሩበት አሰራር እንዳለ ጠቁመው፣ በዚህ መልኩ ሲሰራ በነበረ አንድ ድርጅት ላይ የወረዳው ስራ አስፈፃሚ እርምጃ ወስዶበታል ብለዋል፡፡

Subscribe or Rent movies to watch. Monthly Subscription - 20 አዳዲስ + 6 ተጨማሪ ፊልሞች በየወሩ እና ከዚህ በፊት የተለቀቁ ከ400 በላይ ፊልሞችን ሆነ ሌሎች ቪድዮዎችን በፈለጋችሁት ሰዓት፣ ያሻችሁን ያህል ደጋግማች በቲቪ፣ ተንቀሳቃሽ ስልክ ወይም ኮምፒውተር ተመልከቱ። የአንድ ወር ከፍላቹህ በፈለጋችሁት ሰዓት ማቋረጥ ትችላላቹህ። Watch 20 new + additional 6 movies per month and more than 400 Ethiopian movies. You can watch when you want, as much as you want on TV, mobile phone, tablet or computer. Subscribe for one month and cancel anytime. Monthly subscription prices are $4.99, $19.99 or $29.99. Rent price starts at $2.99. 29.99/month - 20 new after sign up + 6 new movies per month and 400+ released films የሶደሬ ደንበኛ የምትሆኑት ለመጀመርያ ጊዜ ከሆነ እስከ 20 አዳዲስ ፊልሞች+ 6 ተጨማሪ ፊልሞች በየወሩ እና ከዚህ በፊት የተለቀቁ ከ400 በላይ ፊልሞች KIDS videos የልጆች ቪድዮዎች   Movie premier videos የፊልም ምርቃት ቪድዮውች 19.99/month - 4 new movie after sign up + 4 new movies per month and 400+ released films የሶደሬ ደንበኛ የምትሆኑት ለመጀመርያ ጊዜ ከሆነ እስከ 4 አዳዲስ ፊልሞች + 4 ተጨማሪ ፊልሞች በየወሩ እና ከዚህ በፊት የተለቀቁ ከ400 በላይ ፊልሞች  4.99/month - 2 new movies after sign up + 2 new movies per month and 400+ released films የሶደሬ ደንበኛ የምትሆኑት ለመጀመርያ ጊዜ ከሆነ 2 አዳዲስ ፊልሞች + 2 ተጨማሪ ፊልሞች በየወሩ እና ከዚህ በፊት የተለቀቁ ከ400 በላይ ፊልሞች All videos on SodereTube with no Advertisement ሶደሬቲዩብ ላይ ያሉ ሁሉንም ቪድዮችን ያለ ማስተወቂያ ማየት ይቻላል There are three options to pay: PayPal, credit card or Bank Transfer. ክፍያውን በሶስት መንገድ መክፈል ይቻላል - በፔይፓል፣ ክሬዲት/ዴት ካርድ ወይም በባንክ ቁጥር ማስተላለፍ። To pay through credit card or PayPal, click SUBSCRIBE NOW button, add cart and "proceed to check out", Enter your name, address and other information. ለመክፈል ሰማያዊውን ተጫኑ፣ አድ ቱ ካርት፣ ፕሮሲድ ቱ ቼክ አውት ከዚያ ስማችሁን፣ አድራሻ፣ የፔይፓል ወይም የካርድ መረጃውን አስገቡ። subscribenow Rent and Watch. Price starts at $2.99. ተከራይቶ ለማየት If you pay with bank deposit, you have to pay $100 which allow you to be a subscriber for 3 months and $10 processing fee. To pay using bank deposit, click here. ክፍያ ላይ ችግር ካጋጠማቹህ በዚህ ስልክ ቁጥር ደውሉ። Questions? call 1 310 570 9291 viber or direct. For detailed description and list of movie on SodereOnDemand read this. ስለ ሶደሬ ኦን ዲማንድ የበለጠ ለማወቅ ይህን መረጃ አንብቡ።

Receive Ethiopian News, Movies and Videos by email. Sign up for Email alerts

ትኩስ እና ሰበር ዜና፣ በብዛት የታዩ ቪድዮዎች፣ ፊልሞች፣ ድራማዎች፣ ሙዚቃዎች፣ ጠቃሚ ምክሮችን እና አስገራሚ ታሪኮችን በቀን አንዴ በኢሜል አድራሻችሁ እንልካለን።