Written by  ፈለቀ አበበ arthabesha@gmail.com

ውድ አንባቢያን፤ ባለፈው ሳምንት ‹‹እጹብ ድንቅ ጥበብ! – ብርቱ ጠኔ! – (የተአምረኛው የሙዚቃ ጠቢብ ገድል ) በሚል ርዕስ በቀረበው ጽሑፍ መካከል፤ ለሞዛርት (የራሱ ሳያንሰው) ከሥመ ጥሩ የሙዚቃ ሰው ዲቮራክ Dvorak የስጋ ነጋዴ ልጅነትን ቆንጥሮ የማዋስ የተራኪ ቱሩጁማንነት ድንገቴ መዳለጥ (slip) ክስተት፤ ለዚህ ሳምንት የጽሑፍ ምርጫ እንደ መነሻ ሰበብ ሆኗል፡፡ ሊቃውንቱንም ያጋጥማቸዋል ለማለት ያህል እነሆ . . .
ከጥቂት አመታት በፊት፤ ደቡብ ጀርመን በሚገኝ አነስተኛ ከተማ መካከል ሳቋርጥ፤ አብሮኝ የነበረው ወዳጄ ድንገት እርምጃዬን ገትቶ፤ወደ አንዲት ከግሮሰሪ በላይ ያለች መኖሪያ ፎቅ ቤት መስኮት እየጠቆመኝ፤ ‹‹ያቺን አፓርትመንት አየሀት አይንስታይን የተወለደባት ቤት ናት›› አለኝ።
በዚያው እለትም የአይንስታይንን አጎት አግኝቼ አነጋገርኳቸው፡፡ ነገር ግን በሰውየው ላይ፤ እንደ አንድ ልዩ የአዕምሮ ተሰጥኦ ባለቤት የሆነ ሰው አጎት የሚያስቆጥራቸው አንዳችም ልዩ መስህብ አላስተዋልኩባቸውም፡፡ በእርግጥ ይህ ብዙም የሚያስገርም ላይሆን ይችላል፡፡ ለምን ቢሉ፤ ራሱ አልበርት አይንስታይንም ያኔ ገና በልጅነቱ ሲያዩት፤ በኋላ ለደረሰበት ላቅ ያለ ደረጃ ይበቃል ብሎ የሚያስበው አልነበረምና፡፡ እርሱ ግን በዘመኑ ከኖሩቱ ጥልቅ አሰላሳይ ምሁራንና ሊቃውንቱ ሁሉ የመጠበብ ብቃትን ያለ ገደብ የተቸረ የተለየ ልእለ ሰብእ ሆነ፡፡ ከትውልዱ መካከል ነጥሎ ከፍተኛውን ‹የመቼውም ጊዜ አዋቂ› ስያሜ ያቀዳጀው የማገናዘብና የመመራመር ተሰጥኦና ክህሎቱ ልቀት መጠን፣ ወርድና ስፋቱ ጽንፍ የለሽ የተሰኘ ረቂቅ ባለ አእምሮ ሰው፡፡ ስድሳ አመታት አስቀድሞ ግን አይናፋርና ዝግ ያለ፡ ቀሰስተኛ ልጅ ነበረ፡፡ አፉን ለመፍታት እንኳን ቡዙ ጊዜ ወስዶበታል፡፡ ቅልጥፍና ስለሚጎድለውም አስተማሪዎቹ ለንቋሳ ተማሪ ብለው ሲጠሩት፤ ወላጆቹም እንዲሁ፤ ሲወለድ ጀምሮ የተጠናወተ ጎዶሎ ተፈጥሮ እንዳይጣባው በስጋት ተወጥረው ቆይተዋል፡፡
አይንስታይንም ቢሆን በአለሙ ዙሪያ ስመ ጥር ከሆኑት ሰዎች አንዱ የመሆኑ ጉዳይ በእጅጉ ያስደምመው ነበር፡፡ አንድ የሂሳብ መምህር እንዲህ በመላ ምድሪቱ በሚገኙ አምስቱ አህጉራት ሁሉ በሚታተሙ የጋዜጣና መጽሄቶች የፊት ገጽ ላይ ዜና ሆኖ ምስሉ መውጣቱ ፍጹም ለማመን የሚቸግር ነበር፡፡ በባህርይውም ልክ እንደ የራሱ የቀመር ግኝት እንደ አንጻራዊነት ንድፈ ሀሳብ (Theory of Relativity) ያለ ግራ የሚያጋባ አይነት ነበር ለማለት ይቻላል፡፡ በኑሮው፤ የአብዛኛውን ሰው ቀልብ በሚነሱት፡- እንደ ሀብት፣ ዝና ፈላጊነትና ቅንጦት ጉዳዮች ብዙም፣ የሚያስጨንቁት ሰው አልነበረም፡፡ ለምሳሌ ባንድ ወቅት የትራንስ-አትላንቲክ መርከብ ካፒቴን አንደኛ ማእረግ በሆነው በልዩ ክፍል ውስጥ ይሆን ዘንድ ሲጋብዘው፤ የቀረበለትን የክብር ግብዣ ጥያቄ ውድቅ አድርጎ፤ እንደ ማንኛውም ተሳፋሪ በተራው ክፍል ውስጥ ተቀምጦ መጓዝ እንደሚፈልግና ከሌሎች ተሳፋሪዎች የተለየ አንዳችም አይነት ልዩ እንክብካቤ እንደማይፈልግ ቁርጥ ያለ፡ ያልተጠበቀ ምላሽን ሰጥቶ ያውቃል፡፡
አይንስታይን ሃምሳኛ አመት እድሜውን ሲደፍን፤ ሀገረ ጀርመን በደማቅ ክብር አሸበረቀችው፤ ለመታሰቢያውም ፖስትዳም በተባለ ስፍራ ሀውልት (Bust) ቆመለት፤ ስለ ታላቅ ዜጋነቱም የመላውን ህዝብ ፍቅር ማሳያና ለዘወትር የማይነጥፍ ለተባለለት ሞያዊ አሻራው ቋሚ መዘክር ሆኖ የሚቆጠርም የመኖሪያ ቤትና በግሉ የሚቀዝፋት ውድ ጀልባ በስጦታ ተበረከቱለት፡፡
ጥቂት አመታት ቆይቶ ግን ያለው ሀብትና ቅርስ ሁሉ ተወርሶ ወደ ትውልድ ሀገሩ ለመመለስ የማይችልበት ሁኔታ ውስጥ ራሱን አገኘው፡፡ ለሳምንታት ያህልም በቤልጅየም አንድ ኦና ቤት ውስጥ ለመኖር ተገደደ፡፡ በየሌሊቱም በአይነ ቁራኛ የሚጠብቀው ዘብ በራፉ ላይ ይተኛ ነበር፡፡
ለማቲማቲክስ ፕሮፌሰርነት ተጨማሪ ጥናትና ምርምር ለማድረግ ወደ ኒውዮርክ ፕሪንስተን ተቋም በሄደ ጊዜም፤ ከጋዜጠኞች ቃለ መጠይቅና ግርግር ራሱን ለመሸሸግ ጥረት ያደርግ ጀመር፡፡ በዚህም አንዳንድ ወዳጆቹ በመግቢያና መውጫ ሰአቶቹ እየተገኙና ከመገናኛ ብዙሀን ሰዎች እይታ ደብቀው በማመላለስ ተባብረውታል፡፡
አይንስታይን እንዳለው ከሆነ፤ የአንጻራዊነት ንድፈ ሀሳቡን Theory of Relativity ቀመር የተረዱለት አስራ ሁለት ሰዎች ብቻ ነበሩ፡፡ ሆኖም ቀመሩን ተንትኖ ለማስረዳት በንድፈ ሀሳቡ ዙሪያ የሚያጠነጥኑ ከዘጠኝ መቶ በላይ መጻሕፍት ተጽፈዋል፡፡
እሱ ራሱ ሬላቲቪቲን እንዲህ ሲል በቀላል ምሳሌ ይገልጸዋል፡፡ ‹‹ከአንዲት ቆንጆ ሴት ጋር ለአንድ ሰአት ያህል አብረሀት ስትቀመጥ አንዲት ደቂቃ ብቻ የቆየህ ይመስልሀል፤ በአንድ የጋለ ብረት ምጣድ ላይ ለአንዲት ደቂቃ ብትቀመጥ ግን የአንድ ሰአት ያህል ይረዝምብሀል፡፡
‹‹በቃ እንግዲህ ሬላቲቪቲ ማለት ይኸው ነው። ለኔ በበኩሌ ይስማማኛል፤ ላንተ ካልመሰለህና ማረጋገጥ ካሻህ ግን፤ እኔ ከቆንጅዬዋ ሴት ጋር። አንተ በጋለው ብረት ምጣድ ላይ ተቀምጠን ብንሞክረው ደስታውን አልችለውም፡፡››
አይንስታይን ሁለት ጊዜ ትዳር መስርቷል። ከመጀመሪያ ትዳሩ ሁለት ልጆችን ያፈራ ሲሆን፤ እነርሱም የአባታቸው አዋቂነት የሚንፀባረቅባቸው አስተዋዮች ነበሩ፡፡
ሚስቱ በበኩሏ፤ ምንም እንኳ እሷም ብትሆን ስለ የአንጻራዊነት ንድፈ ሀሳቡ ግንዛቤው እንደሌላት ባትሸሽግም፤ ከዚያ የሚበልጠውን ጉዳይ ግን ጠንቅቃ እንደምትረዳ ታምናለች፤ ይኸውም አንዲት ሚስት ለባሏ መመቸት እንደሚገባትና ፍላጎቱን መረዳት የሚጠበቅባት መሆኑን ነው፡፡
አልፎ አልፎ ጓደኞቿን ቤቷ ሻይ ጋብዛ፤ ፕሮፌሰሩ ወደ ታችኛው ቤት እንዲመጣና እንዲያገኛቸው ስትጠይቀው ‹‹እምቢ!›› ብሎ ይቃወማታል፡፡ ‹‹እምቢ! አልመጣም! አልመጣም! በቃ ከዚህ ቤት መሄድ አለብኝ! እዚህ ሆኜ መስራት አልቻልኩም! በዚህ ሁኔታ ከስራዬ እየተናጠብኩ መቆት አልፈልግም፡፡››
ወይዘሮ ፍራዉ አይንስታይን ታዲያ፤ ባል ሆዬ ላፍታ በንዴት እርር ድብን ጭስስ ብሎ እስኪያበቃ ትጠብቀውና፤ አግባብታ ወደ ታችኛው ክፍል ይዛው ወርዳ ሻይ እንዲጠጣ፡ ለስራውም ስኬት የሚያግዘውን ጥቂት እረፍት እንዲያገኝና ዘና እንዲል ታደርገዋለች፡፡
ፍራዉ አይንስታይን፤ ባለቤቷ የምርምር ስራውን በተመለከተ ለስርአት ተገዢ ቢሆንም በእለት ተዕለት ኑሮው ግን አሻፈረኝ ባይ ነው ትላለች፡፡ ማድረግ የሚፈልገውን ነገር ሁሉ ማድረግ ነው የሚሻው፤ ለማድረግ ባሰኘው ጊዜ ሁሉ፡፡ እናም የህይወቱ መርህ የሆኑ ሁለት አቢይ አቋሞች ብቻ አሉት፡፡ የመጀመሪያው፤ ምንም አይነት አስገዳጅ ደንቦች አይኑሩህ፡፡ እና ሁለተኛው፤ የሌሎች ሰዎች አመለካከት ጥገኛ አትሁን፡፡
ቀለል ያለ ህይወትን ነበር የሚኖረው፡፡ በመንገድ ላይ ሲንሸራሸር ካውያ የተራቡ ጨምዳዳ አሮጌ ልብሶችን ሊለብስ ይችላል፡፡ አናቱ ላይ ቆብ ጣል የሚያደርግበት ጊዜም አለ፡፡ መታጠቢያ ቤት ውስጥ ሲሆን ያፏጫል፤ ያንጎራጉራል፤ ከገንዳው ሳይወጣም ጢሙን ይላጫል፡፡ የተለየ የጢም መላጫ ሳሙናም አይፈልግም፡፡ በዚያው ገላውን በታጠበበት ሳሙና ይጠቀማል እንጂ፡፡ ይኼ የመላ ህዋውን ቅጣምባሩ የጠፋ እንቆቅልሽ ለመፍታት የታተረ ሰው፤ ሁለት የተለያዩ ሳሙናዎችን መጠቀም ህይወትን ክፉኛ ያዘበራርቃል ይላል፡፡
ከአይንስታይን የወደድኩለት ነገር ቢኖር፤ ደስተኛ ሰው መሆኑን ነው፡፡ ስለ ደስታ ያለው ፍልስፍናውም ከአንጻራዊነት ንድፈ ሀሳቡም በላይ ነው ለኔ፡፡ እፁብ ድንቅ ፍልስፍና መሆኑም ይሰማኛል፡፡ ደስተኛ የሆነበት ምክንያት ከማንም ምንም የማይፈልግ በመሆኑ ነው፡፡ ገንዘብ፣ ማእረግ ወይም ምስጋናን አይፈልግም፡፡ ደስታውን የሚሸምትባቸው ሀብቶቹም ስራውን ማከናወን፡ ቫዮሊኑን መጫወትና ጀልባውን መቅዘፍ ናቸው፡፡
በተለይ ቫዮሊኑን መጫወት በህይወቱ ከምንም በላይ ደስታ ማግኛው ሲሆን፤ እሱም እንደሚለው በአመዛኙ ስለ ጥናትና ምርምሩ የሚያውጠነጥነውና የየቀኑን ህልምና ቅዠቶቹን የሚኖራቸውም በሙዚቃ ሞገድ እየተንሳፈፈ ነበር፡፡
አንድ ቀን፤ በርሊን ውስጥ በህዝብ ማመላለሻ አውቶብስ ተሳፍሮ፤ ለቲኬት ቆራጩ፤ ‹‹የሰጠኸኝ መልስ ተሳስቷል›› አለው፡፡ ቲኬት ቆራጩ መልሱን ተቀብሎ ደግሞ ሲቆጥረው ግን ትክክል ሆኖ አገኘው። እናስ ገንዘቡን መልሶ እጁ ላይ እያስቀመጠለት አይንስታይንን ምን ቢለው ጥሩ ነው ‹‹ጌታው፤ የእርስዎ ችግር ፤ሂሳብ አለማወቅዎ ነው!››

Subscribe or Rent movies to watch. Monthly Subscription - 20 አዳዲስ + 6 ተጨማሪ ፊልሞች በየወሩ እና ከዚህ በፊት የተለቀቁ ከ400 በላይ ፊልሞችን ሆነ ሌሎች ቪድዮዎችን በፈለጋችሁት ሰዓት፣ ያሻችሁን ያህል ደጋግማች በቲቪ፣ ተንቀሳቃሽ ስልክ ወይም ኮምፒውተር ተመልከቱ። የአንድ ወር ከፍላቹህ በፈለጋችሁት ሰዓት ማቋረጥ ትችላላቹህ። Watch 20 new + additional 6 movies per month and more than 400 Ethiopian movies. You can watch when you want, as much as you want on TV, mobile phone, tablet or computer. Subscribe for one month and cancel anytime. Monthly subscription prices are $4.99, $19.99 or $29.99. Rent price starts at $2.99. 29.99/month - 20 new after sign up + 6 new movies per month and 400+ released films የሶደሬ ደንበኛ የምትሆኑት ለመጀመርያ ጊዜ ከሆነ እስከ 20 አዳዲስ ፊልሞች+ 6 ተጨማሪ ፊልሞች በየወሩ እና ከዚህ በፊት የተለቀቁ ከ400 በላይ ፊልሞች KIDS videos የልጆች ቪድዮዎች   Movie premier videos የፊልም ምርቃት ቪድዮውች 19.99/month - 4 new movie after sign up + 4 new movies per month and 400+ released films የሶደሬ ደንበኛ የምትሆኑት ለመጀመርያ ጊዜ ከሆነ እስከ 4 አዳዲስ ፊልሞች + 4 ተጨማሪ ፊልሞች በየወሩ እና ከዚህ በፊት የተለቀቁ ከ400 በላይ ፊልሞች  4.99/month - 2 new movies after sign up + 2 new movies per month and 400+ released films የሶደሬ ደንበኛ የምትሆኑት ለመጀመርያ ጊዜ ከሆነ 2 አዳዲስ ፊልሞች + 2 ተጨማሪ ፊልሞች በየወሩ እና ከዚህ በፊት የተለቀቁ ከ400 በላይ ፊልሞች All videos on SodereTube with no Advertisement ሶደሬቲዩብ ላይ ያሉ ሁሉንም ቪድዮችን ያለ ማስተወቂያ ማየት ይቻላል There are three options to pay: PayPal, credit card or Bank Transfer. ክፍያውን በሶስት መንገድ መክፈል ይቻላል - በፔይፓል፣ ክሬዲት/ዴት ካርድ ወይም በባንክ ቁጥር ማስተላለፍ። To pay through credit card or PayPal, click SUBSCRIBE NOW button, add cart and "proceed to check out", Enter your name, address and other information. ለመክፈል ሰማያዊውን ተጫኑ፣ አድ ቱ ካርት፣ ፕሮሲድ ቱ ቼክ አውት ከዚያ ስማችሁን፣ አድራሻ፣ የፔይፓል ወይም የካርድ መረጃውን አስገቡ። subscribenow Rent and Watch. Price starts at $2.99. ተከራይቶ ለማየት If you pay with bank deposit, you have to pay $100 which allow you to be a subscriber for 3 months and $10 processing fee. To pay using bank deposit, click here. ክፍያ ላይ ችግር ካጋጠማቹህ በዚህ ስልክ ቁጥር ደውሉ። Questions? call 1 310 570 9291 viber or direct. For detailed description and list of movie on SodereOnDemand read this. ስለ ሶደሬ ኦን ዲማንድ የበለጠ ለማወቅ ይህን መረጃ አንብቡ።

Receive Ethiopian News, Movies and Videos by email. Sign up for Email alerts

ትኩስ እና ሰበር ዜና፣ በብዛት የታዩ ቪድዮዎች፣ ፊልሞች፣ ድራማዎች፣ ሙዚቃዎች፣ ጠቃሚ ምክሮችን እና አስገራሚ ታሪኮችን በቀን አንዴ በኢሜል አድራሻችሁ እንልካለን።